ኢትዮጵያ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች ከሞሮኮ ጋር ጠንካራ ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

137

አዲስ አበባ፡ ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሞሮኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር ተወያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያን እና ሞሮኮን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል፡፡

በውይይቱም ኢትዮጵያ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች ከሞሮኮ ጋር ጠንካራ ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ አቶ ደመቀ ገልጸዋል፡፡

ከሞሮኮ ጋር በሁለትዮሽ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከርም ውይይት መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከ40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን እንደቀጠሉ ነው።

35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዳያስፖራዎች በኮምቦልቻ ከተማ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው እና በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next articleማዕድን ሚኒስቴር በአማራ ክልል በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።