ዳያስፖራዎች በኮምቦልቻ ከተማ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው እና በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

120

ደሴ፡ ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባሰባሰቡት 22 ሺህ ዩሮ በኮምቦልቻ ከተማ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው እና በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች የዱቄት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የዳያስፖራዎቹ ተወካይ አቶ ጌዲዮን ካሁን ቀደም ከ700 ሺህ ብር በላይ በማውጣት በአጣየ ከተማ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በኮምቦልቻ እና አካባቢውም ከ450 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው እና በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

የአረንቻታ ሚዲያ ባለቤት እና የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ጀማል ሰይድ (ቻቻ) የዳያስፖራውን ማኅበረሰብ በማኅበራዊ ሚዲያ በማግኘት ለድጋፉ ማስተባባር መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ ድጋፉም ለወገናችን አለኝታነታችንን የምናሳይበት ነው ብለዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች “በችግራችን ወቅት የዳያስፖራው ማኅበረሰብ ስለደረሰልን እናመሰግናለን” ሲሉ ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ሐበሻ አንለይ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየሰሜን ምዕራብ ዕዝ በኅልውና ዘመቻው ወቅት የላቀ የግዳጅ አፈጻጸም ላሳዩ የሠራዊት አባላት የእውቅና ሥነ ሥርዓት እያካሄደ ነው፡፡
Next articleኢትዮጵያ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች ከሞሮኮ ጋር ጠንካራ ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።