“መንግሥት በቦረና ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ጉዳት በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

92

ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት በቦረና ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ጉዳት በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ተግባራትን እንደሚያከናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦረና ዞን በመገኘት ድርቅ ያስከተለውን ጉዳት ተመልክተዋል፡፡ በዞኑ የሚገኘውን የቦረና ከብት ዝርያ ማራቢያ እና ማስፋፊያ ማዕከልንም ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝቱም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መንግሥት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እያቀረበ ካለው የዕለት ደራሽ ድጋፍ ባሻገር ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ያደርጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቦረና ዞን እየተገነቡ ያሉ አነስተኛ ግድቦችን በአብነት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህም በዞኑ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ድርቅ የሚያስከትለውን ጉዳት በዘላቂነት መፍታት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው የክልሉ መንግሥት በዞኑ እየተገነቡ ያሉ አነስተኛ ግድቦችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ አገልግሎት እንዲሰጡ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የተናገሩት ደግሞ የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጃርሶ ቦሩ ናቸው፡፡

መንግሥት የእንስሳት መኖን ጨምሮ የተለያዩ የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ እያደረገ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዞኑ እያደረጉት ባለው ጉብኝት በያቤሎ ከተማ የተገነባውን ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትንም ተመልክተዋል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ አርብቶ አደሮች የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ።
Next articleየሥራ ፈጣሪዎች የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች ተቋቁመው ባላቸው ዕውቀት ራሳቸውንና ሀገራቸውን ለመጥቀም ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ተናገሩ፡፡