የአማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ አርብቶ አደሮች የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ።

395

ጥር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ አርብቶ አደሮች የእንስሳት መኖ ድጋፍ አድርጓል።

የተደረገው ድጋፍ ከአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ የተሰበሰበ ነው። ድጋፉንም በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ በመገኘት የአማራ ክልል የሀገር ሽማግሌዎችን የወከሉና የክልሉ መንግሥት አካላት ለዞኑ አስረክበዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሰላም ዋሪዎ እንደተናገሩት የአማራ ሕዝብና መንግሥት ችግር ውስጥ እያለ የቦረና የድርቅ ችግር የኔም ችግርና ሕመም ነው ብሎ ድጋፍ በማድረጉ ትልቅ ክብርና ቦታ የምንሰጠው ነው፤ ለአለኝታነቱ እናመሰግናለን ብለዋል።

የክልሉን መንግሥት በመወከል ድጋፉን ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ያስረከቡት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ በበኩላቸው የአማራ ክልል ምንም እንኳ በጦርነቱ የተጎዳ ቢሆንም በቦረና ዞን በድርቁ እየሞቱና እየተጎዱ ያሉ እንስሳትን መታደግ አስፈላጊና ጊዜ የማይሰጠው በመሆኑ በኢትዮጵያዊ አንድነትና ወንድማማችነት መንፈስ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ድልነሳ መንግሥቴ – ከያቤሎ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተቀዛቀዘውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ መልሶ ለማቋቋም 154 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ መሃማት ተናገሩ።
Next article“መንግሥት በቦረና ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ጉዳት በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)