በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተቀዛቀዘውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ መልሶ ለማቋቋም 154 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ መሃማት ተናገሩ።

176

ጥር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ሕብረት 40ኛው የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።

በስብሰባው መጀመሪያ ላይ የሕብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ መሃማት እንደተናገሩት፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ እድገት ክፉኛ ጎድቶታል ብለዋል።

ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ የአህጉሪቱ ኢኮኖሚው በዚህ ደረጃ ሲጎዳ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ጠቁመው በዚህም በአህጉሪቱ የዋጋ ንረት እንዲከሰት ማድረጉን ገልጸዋል።

ወረርሽኙ ባስከተለው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ በአህጉር ደረጃ ያለው የውጭ የብድር ጫና እንዲከብድ ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተቀዛቀዘውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ መልሶ ለማቋቋም 154 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከአፍሪካ የበሽታ መቆጠጣር ማዕከልና ከአካባቢያዊ የኢኮኖሚ ማኅበራት ጋር በመሆን አመርቂ ሥራ መሠራቱን አንስተዋል።

የኮሮናቫይረስ ምርመራ፣ በቫይሩሱ የታዙ ሰዎች የሚሰጠው ህክምና እና ክትባት የማዳረስ ሥራ በአህጉር ደረጃ አበረታች ደረጃ ላይ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በአሁኑ ወቅተ በአህጉሪቱ የክትባት መጠን ከ10 በመቶ በታች መሆኑን ገልጸው፤ በሀገራቱ የተጀመረው የኮሮናቫይረስ ክትባት የማምረት እንቅስቃሴ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

በባለብዙ ወገን ትብብር መስክ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከልና የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት በጋራ መሥራት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

የባለፈው ዓመት የሕብረቱ መሪ ሐሳብ የነበረው ጥበብ፣ ባሕልና ቅርስ የተመለከቱና በሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ትኩረት እንዲደረግባቸው የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ አበረታች ውጤት መገኘቱንም አንስተዋል።

የአፍሪካ ሕብረት የፋይናንስ ኦዲት ሥራን ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ለመቆጣጠር በሶፍትዌር የተደገፈ ሥራ መከናወኑ ብክነትን በመከላከል ትልቅ ፋይዳ እንዳስገኘ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ቃል በገቡት መሠረት ሕብረቱን ለመደገፍ የሚያዋጡትን መዋጮ የሚፈጽሙ ከኾነ አህጉሪቱን ከውጭ ድጋፍ ማላቀቅ ይቻላል ብለዋል፤ ይህንንም ለማድረግ የማስተባበር ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፍሪካ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የተደገፈ የትምህርት ሥርዓት እንዲዘረጋ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

የግብርናውንም ዘርፍ ለማዘመን እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል አፍሪካ በአንዳንድ ሀገራት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየያ ያለው ኢ-ሕገ መንግሥታዊ የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ የሀገሪቱን የሰላምና ደኅንነት ሁኔታ እየጎዳው መሆኑን ገልጸዋል።

በአህጉሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ለበርካታ ሰዎች ህልፈትና ስደት ምክንያት መሆኑን በመግለጽ ሀገራት ሕብረቱ ያስቀመጠውን የሰላም መመሪያ ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአፋር ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ።
Next articleየአማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ አርብቶ አደሮች የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ።