
ጥር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከካሜሮኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌዡን ምቤላ ምቤላ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የተካሄደው ከ40ኛው የአፍሪካ ሕብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ጎን ለጎን ነው።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ካሜሮን በጀኔቫው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ወቅት ለኢትዮጵያ ድጋፍ በማድረጓ ምሥጋናቸውን ገልጸዋል።
የካሜሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌዡን ምቤላ ምቤላ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተለያዩ መስኮች አጠናክሮ ለማስቀጠል ሀገራቸው ፍላጎት ያላት ስለመኾኑ ተናግረዋል።
በኹለቱ ሀገራት መካከል የፖለቲካ ምክክር ብሎም በግብርና ዘርፍ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው የካሜሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/