“የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

112

አዲስ አበባ፡ ጥር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታዋ እንደገለጹት የሕብረቱ የሚኒስትሮች ስብሰባ ለ40ኛ ጊዜ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። ዋናው የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሚመራው (ካዴፕ) የተሰኘ ፕሮግራም በኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ሪፖርት ያቀርባል። ሌሎችም ፕሮግራሞች ይገመገማሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

እንግዶች በሰላም እንዲመለሱ ለማድረግ የደኅንነት እና የፀጥታ ሥራዎች በአግባቡ እየተሠሩ መሆኑን አንስተዋል። እስከአሁን የገቡ መሪዎች አዲስ አበባ ሲወራባት እንደነበረችው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሳትሆን ሰላማዊ ናት እያሉ እየገለፁልን ይገኛሉ ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ። የኮሮናቫይረስ ምርመራን በሚመለከት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የኮሮናቫይረስ ፕሮቶኮሉን በሚገባ እያስተገበረ መሆኑን ወይዘሮ ሰላማዊት ጠቅሰዋል። የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ፕሮቶኮልን በመጠበቅ ኅብረተሰቡ እንዲተባበርም ጥሪ ቀርቧል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ በመግለጫቸው እንዳነሱት የሰብዓዊ ድጋፍን በሚመለከት ካለፉት 10 ዓመታት ወዲህ የከፋ የሚባል ድርቅ በኢትዮጵያ ተከስቷል፤ በእንስሳት ላይ ያጋጠመው የሞት አደጋ በዜጎች ላይ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሠራ ነው፤ አሁንም በሶማሌ ክልል ብቻ 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ሕዝብ ድጋፍ ይፈልጋል። የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ በማድረግ ጉዳቱን ለመቀነስ 255 ሚሊየን ብር ድጋፍ ከአጋዥ አካላት እንደተገኘ እና በሶማሌ ክልል የቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እየተሞከረ ነው ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ለ166 ሺህ ሰዎች የዕለት ምግብ እየቀረበ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ በምሥራቅ ባሌ ደግሞ ይህን ድጋፍ ለማጠናከር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን 77 ሺህ ዜጎች እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛሉ። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ድጋፍ በማድረጉ ጥረት እንዲሳተፍ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ፡-አንዱዓለም መናን-ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።
Next articleካሜሮን ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ መስኮች ትብብሯን አጠናክራ ለማስቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገለጸች፡፡