ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።

125

አዲስ አበባ፡ ጥር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ከደቂቃዎች በፊት ተጀምሯል።

በመድረኩም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ “የአፍሪካ አህጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ማፋጠን” በሚል መሪ መልዕክት ይመክራል።

የአስፈጻሚ ምክር ቤቱ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በሚካሔደው 35ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይም ይወያያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት በሕብረቱ አባል ሀገራት የጋራ ፍላጎት የሆኑ የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚያስተባብርና ውሳኔ የሚሰጥ ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአማራ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ አደረገ።
Next article“የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት