የአማራ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ አደረገ።

322

ጅግጅጋ፡ ጥር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚኾን የእንስሳት መኖ ድጋፍ አድርጓል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በሶማሌ ክልል የተከሰተውን የድርቅ ችግር በጋራ ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ የአማራ ክልል ችግር በገጠመው ወቅት የሶማሌ ክልል ከጎኑ እንደነበር አንስተዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ ለተደረገላቸው አቀባበል ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

ለአንድነታችን በጋራ መሥራት ይገባናል ያሉት ዶክተር ይልቃል የሶማሌ ወንድሞቻችን የድርቅ አደጋ የኹላችንም ቁስል በመሆኑ አይዟችሁ ልንላቸዉ ይገባልም ሲሉም ገልጸዋል። “በጋራ መቆም በሚያስፈልገበት ወቅት በጋራ ቆመናል፤ በዚህም ድጋፍ የአንድነት ተምሳሌትነታችንን አሳይተናል” ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ድርቅ በተከሰተበት አካባቢ የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ እያደረገዉ ያለዉ ጥረት ያስመሰግናልም ነው ያሉት፡፡

የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አማራ ክልል በአሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ቢደርስበትም ክልሉ ድጋፍ ማድረጉ አንድነታችንን እና መተሳሰባችንን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ካሁን ቀደም በነበረው ሥርዓት ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ቢሠራም አኹን ሀገራዊ አንድነትን የሚያሳይ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

አብሮ የመኖርና የመተባበር እሴት እየቀጠለ እንደሚገኝ የገለጹት ርእሰ መሥተዳድሩ በጦርነቱም በጋራ በመቆም ድል መገኘቱን አስታዉሰዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ የአማራ ክልል ላደረገዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በሶማሌ ክልል ከ11 ዞኖች በ9 ዞኖች ላይ ድርቅ መከሰቱ የሚታወስ ነው

ዘጋቢ፡-ኤልሳ ጉዑሽ-ከጅግጅጋ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺደብረ ታቦር በአጅባር ሜዳ ሰማይ ሥር”
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።