
ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የፈረንሳይን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ፍሬድሪክ ክላቬዬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት ረጅም ጊዜን ያስቆጠረ መኾኑን አውስተዋል፡፡ በቀጣይ በኹለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት መኖሩን አስረድተዋል፡፡ የፈረንሳይ መንግሥት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ ሚዛናው በኾነ መልኩ መመልከቱም የሚበረታታ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታም አቶ ደመቀ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በመንግሥት በኩል ሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽ ለማድረግ ቁርጠኝነት ያለ ቢኾንም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች እያደረሰ ባለው አዲስ ጥቃት ምክንያት እክል እየፈጠረ መኾኑን አብራርተዋል፡፡
የፈረንሳይ ልዩ መልዕክተኛው አምባሳደር ፍሬድሪክ ክላቬዬ ኢትዮጵያ በአካባቢው ጠንካራ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ለሚያደርገው ጥረት የፈረንሳይ መንግሥት ድጋፍን እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ ኹሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር ለማካሄድ ለሚደረገው ውይይትም መንግሥታቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ልዩ መልዕክተኛው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/