የገቢዎች ሚኒስቴር በመንፈቅ ዓመቱ 171 ነጥብ 31 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

105

ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢዎች ሚኒስቴር በመንፈቅ ዓመቱ 171 ነጥብ 31 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው አስታውቀዋል፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ከሀገር ውስጥ ታክስ እና ከወጭ ንግድና ቀረጥ 185 ነጥብ 78 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በመንፈቅ ዓመቱ 171 ነጥብ 31 ቢሊዮን መሰብሰብ መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

በመንፈቅ ዓመቱ የተሰበሰበው የገቢ መጠንም የዕቅዱ 92 ነጥብ 21 በመቶ መኾኑንም ገልፀዋል፡፡ አፈፃፀሙም ካለፈዉ በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ22 ነጥብ 21 ቢሊዮን ብር ብልጫ ማሳየቱንም አስታውቀዋል፡፡

የገቢ አሰባሰብ አፈጻፀሙ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ማሳየቱንም አመላክተዋል፡፡ የተሰበሰበው ገቢ ከሀገር ውስጥ ታክስ 108 ነጥብ 96 ቢሊዮን ለመሰብሰብ ታቅዶ 105 ነጥብ 37 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ጠቅሰዋል፡፡ በጉምሩክ ደግሞ 76 ነጥብ 83 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 65 ነጥብ 94 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በ 2014 በጀት ዓመት 360 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑም ታውቋል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ከተቋሙ ኃላፊዎችና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጆች ጋር በገመገመበት ወቅት የበጀት ዓመቱን እቅድ ለማሳካት ያስችለኛል ያላቸውን የቀጣይ ወራት የሥራ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል ነው የተባለው፡፡

ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በገቢ አሰባሰቡ የተመዘገበው ውጤት የሚያበረታታ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው ግብር ከፋዮች፣ ሠራተኞች እና ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

 

Previous articleመንግሥትና ሕዝብ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃትና በድል መወጣት የሚያስችል ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ የምሥራቅ ዕዝ ኮር አመራሮች አረጋገጡ፡፡
Next articleየኢትዮጵያ መንግሥት በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረት ፈረንሳይ እንደምትደግፍ ገለጸች፡፡