የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎትን የመረጃ ደኅንነት የሚያስጠብቅ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።

79

ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ፖሊሲው የመንግስት አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ለዜጎች ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመረጃ መረብ ደኅንነትን ለማስጠበቅና በሁሉም ተቋማት ወጥነት ባለው መልኩ ለመተግበር የሚያስችል ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለመሰብሰብ ከፌደራል ተቋማት፣ ከክልልና ከግሉ ዘርፍ ባለድርሻ ጋር እየተወያየ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የመረጃ መረብ ደኅንነት ሥራ አመራር በአግባቡ ካልተመራ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን ስለሚያስከትል ፖሊሲው ይህንን ችግር ለመቅረፍና ወጥ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ያስችላል ብለዋል፡፡

በዓለማችን በተቋማት ላይ በሚፈጸም ጥቃት በደቂቃ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይታጣል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ፖሊሲው ኢትዮጵያ ለዚህ የሚመጥን ዝግጅት ለማድረግ እንደሚርዳት ተናግረዋል።

ፖሊሲው በመንግስት መስሪያ ቤቶች በኩል ለዜጎች፣ ለሠራተኞች፣ ለንግድና ለሌሎች መንግስታዊ ተቋማት የሚዘረጉ መሰረተ ልማቶችና የሚለሙ አገልግሎቶች በመረጃ መረብ ደህንነት ሥራ አመራር ደረጃ ወጥነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ተቋም ዘመናዊ ቤተ መጽሐፍት አስመረቀ።
Next article“ማማው ደብረ ታቦር ታላቁ ታላቁ አይታጠፍ ቃሉ አይፈታም ትጥቁ”