በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ተቋም ዘመናዊ ቤተ መጽሐፍት አስመረቀ።

132
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጅ ተቋም ያስገነባውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ሰጭ የቤተ መጽሐፍት ሕንጻ አስመርቋል። ሕንጻው በውስጡ ቤተ መዘክር፣ የማኅበረሰብ ቤተ መጻሕፍት፣ የተማሪዎች ቤተመጻሕፍት፣ የድሕረ ምረቃ ተማሪዎች፣ የዲጅታል ቤተ መጻሕፍት፣ ካፍቴሪያ እና ሌሎችን አገልግሎቶች ያካተተ ነው ተብሏል።
የቤተ መጽሐፍት ሕንጻው የአካባቢውን እውቀት ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል። ከባሕል ጋር የተያያዙ ፋሽን እና ዲዛይን በዘመናዊ መንገድ ለማስተዋወቅ ይረዳልም ተብሏል።
ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም የተመሠረተበትን 60ኛ ዓመት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ ገልጸዋል።
በምረቃ ሥነስርዓቱ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡-ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleየከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለኹሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።
Next articleየመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎትን የመረጃ ደኅንነት የሚያስጠብቅ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።