
ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱም በተቋማት ተጠያቂነትና የመረጃ ፍሰትን ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ እና ቀልጣፋ ሥራ እንዲያከናወኑ ያስችላል በተባለ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ መዋቅር ላይ ያተኮረ ነው።
በመንግሥትም ኾነ በግል የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ወደሚፈለገው ደረጃ ከፍ ለማድረግ በቀጣይ የትምህርት ዘመን የመውጫ ፈተና ለኹሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ሊሰጥ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርቱ ማኅበረሰብ ከፖለቲካ ነፃ ኾነው ሐሳባቸውን የሚያንሸራሸሩባቸው ተቋማት መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት፣ የምርምርና የአዳዲስ ሐሳቦች መፍለቂያ ከመኾናቸው አንፃር ተልዕኳቸውን በብቃትና በውጤታማነት ለመፈፀም ይችሉ ዘንድ የተጀመረው የመዋቅር ሪፎርም ሥራ አንዱና ወሳኝ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የአካባቢውን ማኅበረሰብ ሕይወት ሊቀይሩ በሚቻሉበት መልኩ ከተልዕኳቸው ጋር አጠናክረው የሚሄዱበትን ጉዳይ ለይተው መሥራት እንደሚገባቸውም መግለጻቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በመርኃግብሩ በተዘጋጀው የዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ መዋቅር ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/