የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

76
አዲስ አበባ፡ ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡ የምክር ቤቱ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳዲስ አባላትን ማጽደቅ እና የምክር ቤቱ የመተዳደሪያ ደንብን ማሻሻያ ማድረግ በጉባኤው የሚነሱ ሐሳቦች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
በጉባዔው ላይ እንደተነሳው መገናኛ ብዙኃን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ተግባራት እንዲሳለጡ ትልቅ አስተዋጾኦ ያበረክታሉ፤ የሐሰት መረጃዎችን በማጋለጥ ወደ ማኅበረሰቡ እውነተኛ መረጃን በማድረስ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ተጠቅሷል፡፡
መገናኛ ብዙኃን በነጻነት እና ገለልተኛ ኾነው እንዲሠሩ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ትልቅ ሚና እንደሚጫዎት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ተናግረዋል።
አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ከሥነ ምግባር የራቁ ተግባራትን ስለሚፈጽሙ ምክር ቤቱ መገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞች በሕግ አግባብ እንዲሠሩ ማድረግ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱ መገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞች በሕጉ መሰረት ሥራቸውን ገለልተኛ በመሆን እንዲሠሩ እና ፖለቲከኞች መገናኛ ብዙኃንን የፖለቲካ ተፅዕኖ መፍጠሪያ እንዳያደርጓቸው ማድረግ እንደሚገባውም ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው- ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/
Previous articleበኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የከተሜነት ህይወት ለማዘመን የዲያስፖራው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
Next articleየከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለኹሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።