
አዲስ አበባ፡ ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ)”በኮንስትራክሽንና ቤቶች ዘርፍ የዲያስፖራው ሚና” በሚል ሃሳብ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ባለስልጣንና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከዲያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ምክክር እያደረጉ ነው። በኮንስትራክሽን ልማት ዘርፍ ያሉ የፖሊሲ ክፍተቶች በምክክሩ ተነስተዋል።
ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ዘርፍ ያልተነካ የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዳላት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ገልጸዋል።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በርካታ ከተሞችን ማውደሙን የገለፁት ሚኒስትሯ የወደሙትን መልሶ ለመገንባት የከተሞች የእህትማማችነት ጥምረት በመፍጠር እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
የወደሙትን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የዲያስፖራው ሚና ከፍተኛ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የከተሜነት ህይወት ለማዘመን የዲያስፖራው ሚና ከፍተኛ መሆኑንና ለዚህ ደግሞ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ይሠራል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።