በአማራ ክልል የአመራር መለየት፣ ማብቃትና የማጥራት ክልላዊ መድረክ እየተካሄደ ነው።

324
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “መመረጥ ተለውጦ ሀገርን መለወጥ” በሚል መሪ መልዕክት ቅድመ ጉባኤ የአመራር መለየት፣ ማብቃትና የማጥራት ክልላዊ መድረክ እየተካሄደ ነው። በየደረጃው የሚገኙ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ መሪዎች እና አባላት፣ የክልል ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በውይይቱ ተገኝተዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጠላት እየቀነስን ወዳጅ እያበዛን መሄድ መቻል አለብን ብለዋል። አንዳንድ ጥያቄዎች በወዳጆቻችን ድጋፍ ጭምር የሚፈቱ ናቸውም ነው ያሉት። ክልሉ ብዙ ውስብስብ ችግር ያለበት፣ የኅልውና ዘመቻው በአግባቡ ያልተጠናቀቀ መሆኑና ብዙ ጥያቄዎች ያልተመለሱ መሆኑ ለመፍትሔው በመግባባት መሥራት ይገባልም ነው ያሉት። ደረጃችን ምን ላይ እንደኾነና ሌሎችም ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ መገምገም ይጠብቀብናልም ብለዋል።
በጠራ አቋምና እምነት ላይ በመቆም መሥራት እንደሚገባም አስታውቀዋል።
የአማራ ክልልን ለመለወጥ እንዘጋጅም ሲሉ አሳስበዋል። አቅም ያለውና የጠራ ኃይል መፍጠር እንደሚገባም ገልፀዋል።
ተመሳሳይ መድረኮች እስከ ፓርቲ መሠረታዊ አደረጃጀቶች እንደሚቀጥልም ታውቋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/
Previous article‹‹በኢትዮጵያ የሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካውያንን አንድነትና ወንድማማችነት ያረጋገጠ ነው›› ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር
Next articleበኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የከተሜነት ህይወት ለማዘመን የዲያስፖራው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡