ግዳጃቸውን በጀግንነት ለተወጡ 150 የምዕራብ ዕዛ አባላት እና አሃዶች የሜዳይ ሽልማት ተበረከተ።

122
ጎንደር፡ ጥር 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ግዳጃቸውን በጀግንነት ለተወጡ የምዕራብ እዝ አባላት በአንደኛ ደረጃ ሜዳይ 29፣ በሁለተኛ ደረጃ ሜዳይ ለ62 እና በሶስተኛ ሜዳይ 59 በግል እና በአሃድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በመርሃ ግብሩ የጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከፍተኛ የምዕራብ ዕዝ አመራሮች ተገኝተዋል።
ከብዙ ጀግኖች መካከል ምርጦችን በመምረጥ የተደረገ ሽልማት ነው ያሉት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ እና የአድዋ ድል ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት ናቸው። በአሃዶች እና በግል የተደረጉ የሜዳይ ሽልማቶች ለቀጣይ ለበለጠ ግዳጅ ወታደሩ እንዲነሳሳ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም መንግሥት ለሚሰጠው ግዳጅ እዙ ዝግጁ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።
ሽልማት የተበረከተላቸው የእዙ አባላት የአየር ጸባይ እና ተፈጥሮ ሳይበግራችሁ ግዳጃችሁን በብቃት በመወጣት ለዚህ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ያሉት የጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ናቸው። ሁሉም በጀግንነት ሲዋጋ እና ሲያዋጋ የተገኘ ድል በመሆኑ በቀጣይም የተሻለ ድል ለሚያስመዘገቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና አሃዶች ሽልማቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው ብለዋል።
ውጊያውን አሸንፈናል ነገር ግን ጦርነቱ አሁንም ያላለቀ በመሆኑ ለቀጣይ ተልዕኮ እዙ መዘጋጀት አለበት ብለዋል።
ሽልማት የተበረከተላቸው የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አባላት የተበረከተላቸው ሽልማት ለቀጣይ ለሚሰጣቸው ግዳጅ እንደሚያነሳሳቸው ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- ዳንኤል ወርቄ – ደባርቅ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ዓ.ም መንፈቅ ዓመት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ።
Next articleወደ ሳዑዲ አረቢያ ያቀናው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተቻለ ፍጥነት ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ መምከሩ ተገለጸ፡፡