ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ዓ.ም መንፈቅ ዓመት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ።

130
አዲስ አበባ: ጥር 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ2014 ዓ.ም የመንፈቅ ዓመት የሥራ አፈጻጸም መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫውም ተቋሙ በመንፈቅ ዓመቱ 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል። የገቢ አፈጻጸሙ የዕቅዱን 86 ነጥብ 4 በመቶ የሸፈነ ነው ብለዋል።
የገቢ ዕቅዱን በመቶ በመቶ መፈጸም ያልተቻለውም በሰሜኑ ክፍል በተከሰተው ጦርነት የተቋሙ ንብረቶች በስፋት በመውደማቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ እና ተንቀሳቅሶ መሥራት ባለመቻሉ ሊገኝ የታቀደውን ገቢ ማግኘት አለመቻሉንም አንስተዋል።
ዘጋቢ:- ራሄል ደምሰው -ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/
Previous articleበቀደመ ከፍታው የቀጠለው ኢትዮጵያዊ ማንነት…
Next articleግዳጃቸውን በጀግንነት ለተወጡ 150 የምዕራብ ዕዛ አባላት እና አሃዶች የሜዳይ ሽልማት ተበረከተ።