“ለትርፍራፊ ጁንታ የሰጠነው የመጨረሻ ሥራ ራሳቸውን ኦዲት እንዲያደርጉ ነው” የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ

297

ወልድያ፡ ጥር 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን በጀግንነት በመዋጋት አስደናቂ ጀብዱ የፈፀሙ የደቡብ እዝ ከፍተኛ አመራሮችና የሠራዊት አባላት የሜዳልያ ሽልማታቸውን ከጦር ኀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ከጀኔራል አበባው ታደሰ እና ከአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ እጅ ተቀብለዋል።

በእውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ እንደተናገሩት ሀገር በፕሮፖጋንዳ እንደማትፈርስ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን እንዲማር ተደርጓል። የሽብር ቡድኑ በተወሰደበት እርምጃ ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ ደርሶበታል፤ እናም “ለትርፍራፊ ጁንታ የሰጠነው የመጨረሻ ሥራ ራሳቸውን ኦዲት እንዲያደርጉ ነው” ብለዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ እንዳሉት አፋር ክልል ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ከትግራይ ክልል ጋር ይዋሰናል። እንደ አፋር መክረን መከላከያን ማገዝ እንዳለብን ተስማምተን የመከላከያ ደጀንነታችንን አጠናክረናል። በውስጥ ክፍፍል ያደገ ሀገር የለም፤ የአማራ ክብር የአፋር ክብር ነው፤ የአፋር ክብር የአማራ ክብር ነው፤ የሁላችን ክብር ደግሞ የኢትዮጵያ ክብር ነው ብለዋል።

ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ ዛሬ ላይ በትላንት ልንማር እንጂ ልንፎክር አይገባም፤ የራሳችንን ታሪክ ሠርተን የምንፎክርበት ጊዜ ስለሆነ እንጠቀምበት፤ የትላንት ታሪካችን ታሪክ የሚሆነው ማስቀጠል ሲቻል ነው፤ የምንፎክርበት ታሪክ የሚሠራው አሁን ነው ብለዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ አሁን አጀንዳችን የውስጥ አንድነታችንን ማስጠበቅ ብቻ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ዘጋቢ:— ካሳሁን ኃይለሚካኤል

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአፄ ቴዎድሮስ መናገሻ የሆነችውን ደረስጌ ማርያምን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
Next articleበኩር ጋዜጣ ጥር 23/2014 ዓ.ም ዕትም