“በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ውድመት የደረሰባቸው ሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ጀምረዋል” የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር

152
ደብረ ብርሃን፡ ጥር 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ በርካታ ተቋማትን አውድሟል። ከወደሙ ተቋማት መካከል የጤና፣ የትምህርት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ይገኙበታል። በዞኑ 183 ትምህርት ቤቶች በዘራፊው ቡድን ከፍተኛ ዘረፋና ውድመት ተፈፅሞባቸዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረ ፃድቅ እነዚህን ትምህርት ቤቶች መልሶ ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል ብለዋል። በተደረገው ርብርብም ሁሉም ትምህርት ቤቶች ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸው ተመልሰዋል ነው ያሉት።
ከወደሙ የትምህርት ተቋማት ባሻገር ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታሎችም ስራ እንዲጀምሩ ተደርጓል ብለዋል። ተቋማቱ ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ በርካታ ወገኖች ርብርብ አድርገዋል ነው የተባለው።
“ተቋማቱ ወደቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ሲባል ሁሉም የተሟላላቸው ሆነዋል ማለት አይደለም” ያሉት ዋና አስተዳዳሪው አሁንም መሟላት ያለባቸው ግብዓቶችን ለማሟላት ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ከህልውና ዘመቻው ጎን ለጎን የመልሶ ግንባታ ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለም አቶ ታደሰ ተናግረዋል። የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ የማቋቋም፣ ከተሞችን የመገንባት፣ ተቋማትንም ስራ የማስጀመር ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
የአካባቢን ሰላም በመጠበቅ ረገድ ለነገ የማይባል ስራ ነው ያሉት አቶ ታደሰ ህብረተሰቡ ከአመራሩ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ነውም ብለዋል።
ከአጎራባች ዞኖችም ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ከአፋር ክልል ዞን አምስት እና ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናገረዋል።
ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጋር የምናደርገው የህልውና ዘመቻ እንዳልተጠናቀቀ በመገንዘብ ከምናለማው ልማት ጎን ለጎን ህልውናችንን ሊያረጋግጥ የሚችል ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የዞኑ ወጣቶች ትላንት በተጀመረው የልዩ ኀይል ምዝገባ ላይ በመሳተፍ ልዩ ኀይሉን እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:–ኤሊያስ ፈጠነ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleʺከአምሳለ አንበሳው እስቴ ዴንሳ ተራራ ግርጌ”
Next articleየአፄ ቴዎድሮስ መናገሻ የሆነችውን ደረስጌ ማርያምን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡