“የአምባሳደሮች ሹመት ሙያዊ ብቃት እና ሀገራዊ ለውጥን መሰረት ያደረገ ነው” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

269

አዲስ አበባ፡ ጥር 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ትናንት ለአምባሳደሮች የተሰጠው ሹመት የግለሰሰቦቹ ሙያዊ ብቃትና ክህሎት እንዲሁም ሀገራዊ ለውጥን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ካነሷቸው ጉዳዩች መካከል፥ ትናንት በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለ27 አምባሳደርሮች የተሰጠውን ሹመት አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሹመቱ ካለፉት ጊዚያት የተለየ እና ጥናትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

በዋናነት የግለሰቦችን ሙያዊ ብቃት፣ ክህሎት እና ሀገራዊ ለውጥን መሰረት ያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

በተጨማሪም ሥራ እና ሠራተኛን በማመጣጠን የተሠራ መሆኑን ጠቁመው፥ በውጭ ጉዳይ ሥራ ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ እንደሚገኙበትም መግለጻቸውን ፋብኮ ዘግቧል።

ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመውሰድም ከሌሎች የሙያ መስኮች ልምድ ያላቸው ግለሰቦችም ተካተዋል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ከተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች መከናወናቸውን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleሀገሪቱ ካለችበት አንጻራዊ ሰላም ጋር ተያይዞ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ከተቀመጠለት የስድስት ወር ገደብ ቀድሞ ማንሳት አስፈላጊ ኾኖ መገኘቱን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
Next articleʺከአምሳለ አንበሳው እስቴ ዴንሳ ተራራ ግርጌ”