
ጥር 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፌደራል መንግሥትና የክልል መንግሥታት የሕግ አስፈጻሚዎች ግንኙነት የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የክልል ርእሰ መሥተዳድሮችና የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች በመድረኩ ላይ ታድመውበታል፡፡
መድረኩ በወቅታዊ የጸጥታና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚመክር ኢብኮ ዘግቧል፡፡ ከዚህ ቀደምም በአማራ ክልል ባሕር ዳር እና አፋር ሰመራ መድረኩ ተካሂዶ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ ውይይቶች ማድረጉም ይታወሳል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/