❝35ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ድል የሚያሳይ ነው❞ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ሰለሞን ተፈራ

242

ጥር 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ቁመና የት እንደረሰ የሚያሳይና የአንዳንድ ምዕራባውያንን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ያጋለጠ መሆኑን በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ሰለሞን ተፈራ ገለጹ።

አቶ ሰለሞን ተፈራ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ አንዳንድ ሀገራት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የሕብረቱ ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ለማድረግ በስፋት ተንቀሳቅሰዋል። ኢትዮጵያ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መደረጉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ቁመና የት እንደረሰ የሚያሳይና የአንዳንድ ምዕራባውያንን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ያጋለጠ ነው ብለዋል።

አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገሮችና የመገናኛ ብዙኀን ተቋሞቻቸው ዜጎቻቸው ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ ሲወተውቱ እና የፕሮፖጋንዳ ጦርነት ሲያካሂዱ ነበር ያሉት መምህሩ 35ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ሲደረግ የነበረው ጥረትም የዚህ ዓለም አቀፍ ጫና አካል ነው። ይህን እኩይ ዓላማቸውን ለማሳካትም አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራትን በመሳሪያት ለመጠቀም መንቀሳቀሳቸውን ጠቁመዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ጥረት ሲደረግ የውጭ ዜጎችና ኤምባሲዎች ኢትዮጵያን ለቀው መውጣት አለባቸው ለሚለው የሐሰት ፕሮፓጋንዳ እንደማረጋገጫ ለመጠቀም ታስቦ እንደነበርም አመላክተዋል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ በኩል በተሠራው ዲፕሎማሲያዊ ሥራ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዲፕሎማሲዊ ድል ያስገኘ መሆኑን አስረድተዋል።

የአፍሪካ መሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማሳየት እድል የሚፈጥር ነው ያሉት የፖለቲካ መምህሩ ፤ አንዳንድ ኤምባሲዎች የሚያወጡት መግለጫም ኾነ ምዕራባውያን ሚዲያዎች ስለኢትዮጵያ የሚዘግቡት ዘገባ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለማሳየትና ሴራቸውን ለማክሸፍ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ መምህሩ ገለጻ፤ ከዋናው የመሪዎች ጉባኤ ባለፈ በሚደረጉ የጎንዮሽ ውይይቶች የሀገሪቱን ዲፕሎማሲያዊ ቁመና ያሳድጋል። የኢትዮጵያ መሪዎች ሀገሪቱ ከማንም ሀገር ጋር ጥል እንደማትፈልግና የምንጊዜም የኢትዮጵያ አቋም የአፍሪካ ችግር በአፍሪካ መፈታት አለበት የሚለው መሆኑን በድጋሚ ማንጸባረቅ እንዳለባት ተናግረዋል።

የሀገር መሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ምንም አይነት ችግር እንዳይፈጠር በጥንቃቄ መሠራት እንዳለበት ያስታወሱት መምህሩ፤ መሪዎች በሰላም መጥተው በጥሩ መስተንግዶ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱና የሀገሪቱ መረጋጋት ምን እንደሚመስል ለማሳየት ሕዝቡም ጭምር ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት ብለዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአማራ ክልል የተከበሩት ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የቱሪዝሙን ዘርፍ በማነቃቃት በኩል ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
Next articleየአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ የቀጣይ ጊዜያት ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት መርኃ ግብር ይፋ አደረገ፡፡