በአማራ ክልል የተከበሩት ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የቱሪዝሙን ዘርፍ በማነቃቃት በኩል ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

119
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ላለፉት ሦስት ዓመታት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ የሕግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ በእጅጉ ጎድተውት ቆይተዋል፡፡ በተለይም የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ የተመሰረቱ አካባቢዎችን የስጋት ቀጠና በማድረጉ ዘርፉ ተዳክሞ ቆይቷል፡፡
ኢትዮጵያዊያን በጋራ በወራሪው ቡድን ላይ ጠንካራ ክንዳቸውን ማሳረፋቸውን ተከትሎ ነፃ በወጡ አካባቢዎች የደረሰውን ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ሃብት ለመተካት በተደረገው ርብርብ የቱሪዝም ዘርፉ የጎላ ሚና ተጫውቷል፡፡ ልደትን በላልይበላ፣ ጥምቀትን በጎንደር፣ ጥርን በባህር ዳር እና መሰል ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ተዳክሞ የነበረውን የክልሉን ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ እንዳነቃቁት የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ምክት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ መኮንን ገልጸዋል፡፡
የወቅቱ የዓለማችን የጤና ስጋት የሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ አዳክሞት ቆይቷል ያሉት አቶ ኤርሚያስ በተለይ ደግሞ የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ዘርፉን የበለጠ ጎደቶታል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን በሽብር ቡድኑ ላይ በወሰዱት ጠንካራ ርምጃ በርካታ የክልሉ አካባቢዎች ከወራሪው ቡድን ነፃ መሆናቸውን ተከትሎ የተከበሩት በዓላት የታለመላቸውን ምጣኔ ሃብታዊ፣ ገጽታ ግንባታ እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ያሳኩ ነበሩ ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም አማራ ክልል ላይ የተረጋጋ ሰላም እንደሌለ አድርገው ሲቀሰቅሱ ለነበሩት የጠላት ግብረአበሮች የበዓላቱ በሰላም መጠናቀቅ የተለየ ምላሽ የሰጠ ነበር ያሉት አቶ ኤርሚያስ ተዳክሞ የነበረውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንዲያንሰራራም እድል ሰጥቷል ብለዋል፡፡
በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ላደረጉ የፌዴራል እና የክልል የጸጥታ ኃይሎች፣ ለክልሉ ሕዝብ እና ወጣቶች የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ላቅ ያለ ምስጋና አለው ብለዋል ምክትል ቢሮ ኃላፊው፡፡ በቀጣይም የአገው ፈረሰኞች ማኅበር በአዊ፣ መርቆሪዎስ በደብረ ታቦር እና አስተርዮ ማሪያም በግሸን ደብረ ከርቤና በመርጡ ለማሪያም እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በድምቀት እንደሚከበሩ የገለጹት አቶ ኤርሚያስ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ በቂ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡
ከውጭ የመጡ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በበዓላቱ ላይ እንዲታደሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ መሰል ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላትን በቅድመ ዝግጅት ታግዞ ማክበር የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን እንደሚያበረታታ ገልጸው በቀጣይ የሚኖሩ ሁነቶችንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ እና እየተጋገዙ ምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳ ባለው መልኩ ይከበራሉ ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleአሸባሪው ህወሓት እንደ አዲስ ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና በቀጣናው የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ክልላዊ መንግስት አሳሰበ፡፡
Next article❝35ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ድል የሚያሳይ ነው❞ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ሰለሞን ተፈራ