
ጥር 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሐንስ ሔንሪክ ጋር በወደሙ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ዙሪያ ውይይት ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ የስዊድን መንግሥት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በርካታ ጥራት ያላቸው ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ መልሶ ለመገንባት መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሐንስ ሔንሪክ በበኩላቸው ሀገራቸው የትምህርት ተቋማትን በጥራት መልሶ ከመገንባት አንፃር ወደፊት ምላሽ እንደምትሰጥ መግለጻቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ የሲዊድን መንግሥት ከ6 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶችን መገንባቱ ይታወቃል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።