የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዙሪያ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

78
ጥር 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የሀገር ኅልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ቁጥር 5/2014 ቀሪ የሚሆንበትን ጊዜ በሚመለከት በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
አሸባሪው ሕወሓት እና ግብረአበሮቹ በሀገራችን ኅልውና እና ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የደቀኑ በመሆኑ እና ይህን አደጋ በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥራ መከላከል የማይቻል ኾኖ በመገኘቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ቁጥር 5/2014ን ያወጀ ሲሆን፣ ይህ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በዐዋጅ ቁጥር 1264/2014 ፀድቆ በሥራ ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ኾኖም ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማውጣት የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑ እና ስጋቱን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 አንቀጽ 11(2) በተደነገገው መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያት የኾኑ ሁኔታዎች ከተቀየሩ እና በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር ይቻላል ብሎ ካመነ የስድስት ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ስልጣን ያለው በመሆኑ የዐዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቦ በውሳኔ ሐሳቡ ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በጥልቀት ተወያይቶ በማጽደቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleበበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከተሰነዘሩ 3ሺህ 406 አደገኛ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ከ96 ከመቶ በላይ የሚሆኑትን ማክሸፉን ኤጀንሲው ገለጸ።
Next articleበአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ መልሶ ለመገንባት የስዊድን መንግሥት እንዲደግፍ ትምህርት ሚኒስቴር ጠየቀ።