በህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካዊያንን አንድነት ይበልጥ በሚያስተሳሰር መልኩ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት ተደርጓል።

201
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የአፍሪካዊያንን አንድነት ይበልጥ በሚያስተሳሰርና የኢትዮጵያን ገጽታ በሚገነባ መልኩ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በአፍሪካ ህብረት መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
ይሁንና ባለፉት ሁለት ዓመታት የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በኮቪድ 19 ወረሽኝ ምክንያት በአካል ማካሄድ ሳይቻል ቀርቷል፡፡
የህብረቱ አባል ሀገራት ከሁለት ዓመታት በኋላ ጉባኤው በአዲስ አበባ እንዲካሄድ የወሰኑ ሲሆን፤ አዲስ አበባም ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን ለመቀበል እየጠበቀች ነው፡፡
ለጉባኤው ስኬት ደግሞ የጸጥታ አካላት፣ ሆቴሎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፣ እንዲሁም የመዝናኛና ቱሪዝም ሥፍራዎች ተግባራዊ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት፤ ለአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የኢትዮጵያን ገጽታ በሚገነባ መልኩ በቂ ዝግጅት ተደርጓል።
ሚኒስቴሩ ቀደም ብሎ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንግዶች በኢትዮጵያ የሚኖራቸውን ቆይታ ስኬታማ ለማድረግ ዝግጅት ማድረጉንም ነው ያነሱት፡፡
ሁቴሎች ከአስጎብኚ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት እንግዶቻቸው በመዲናዋ ያሉ ታሪካዊ ስፍራዎችን በመጎብኘት ኢትዮጵያን እንዲያውቁ የሚያደርጉ ፓኬጆችን ማዘጋጀታቸውንም አብራርተዋል፡፡
በመዲናዋ የሚገኙ ሆቴሎችም የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ገጽታ በሚያስተዋውቅ መልኩ እንግዶቻቸውን ለማስተናገድ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
የዲሊዮፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል የመስተንግዶ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ቃልኪዳን አገርነው የህብረቱን የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ለሚመጡ እንግዶች 40 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል ነው ያሉት፡፡ ኢዜአ እንደዘገበው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleየአጀንዳ 2063 ሰባት አላማዎችና ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫዎች።
Next articleየኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡ ድጋፉ የሚዲያዎችን እርስ በርስ መደጋገፍና ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆምን የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡