የአጀንዳ 2063 ሰባት አላማዎችና ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫዎች።

243
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አጀንዳ 2063 ‘የምንፈልጋትን አፍሪካ‘ በሚል መሪ ሀሳብ አህጉሩ ለ50 ዓመት (ከእ.አ.አ 2013 እስከ 2063) የሚመራበትን እቅድ የያዘ ማዕቀፍ ነው።
አጀንዳ 2063 ሰባት አላማዎችና ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫዎች አሉት። እነሱም፡-
1. ሁሉን አቀፍ በሆነ እድገትና ዘላቂ ልማት የበለጸገች አፍሪካን መፍጠር፤
2. በፓን አፍሪካኒም እሳቤዎችና በአፍሪካ ሕዳሴ ራዕይ አማካኝነት የተሳሰረና ፖለቲካዊ አንድነት ያለው አህጉር እውን ማድረግ፤
3. አፍሪካን መልካም አስተዳደር የሰፈነበት፣ የሰብአዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት የሚከበርበት፣ ፍትሕ የነገሰበትና ዴሞክራሲያዊ አህጉር ማድረግ፤
4. ሰላሙንና አንድነቱን የጠበቀ አፍሪካን መፍጠር፤
5. ጠንካራ የባህል ማንነት፣ የጋራ ቅርስና እሴቶች ያሉት እንዲሁም ጠንካራ ማህበረሳባዊ የሞራል መሰረት የፈጠረ አፍሪካን ማየት፤
6. የአፍሪካ ልማት ዜጎችን ማዕከል ያደረገ፣ የአፍሪካን ሕዝብ በተለይም የወጣቶችና ሴቶችን አቅም የሚጠቀምና ለሕጻናት ክብካቤ ትኩረትን የሰጠ እንዲሆን ማድረግ፤
7. ጠንካራ፣ አንድነቱን የጠበቀ፣ የማይበገርና በዓለም መድረክ ተጽእኖ ፈጣሪና አጋር የሆነ አፍሪካን መፍጠር ናቸው። ኢዜአ እንደዘገበው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Amajjii 15/2014
Next articleበህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካዊያንን አንድነት ይበልጥ በሚያስተሳሰር መልኩ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት ተደርጓል።