
ባሕር ዳር፡ ጥር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ውኃ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰበት የደሴ ከተማ አሥተዳደር ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት የመጀመሪያ ዙር የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ከንብረት ውድመት እስከ ሕይወት መስዋትነት ዋጋ ብንከፍልም በቁጭት ከመሥራት አላገደንም ሲሉ የደሴ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ወርቁ አሞኘ ተናግረዋል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ እንደ ተቋም በዘራፊው እና አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘረፋና ውድመት እንደደረሰበት ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ተስፋየ አቡቡ በተፈጠረው ወረራና ጉዳት አላስፈላጊ ቁጭት ውስጥ መግባት አይኖርብንም በተበረከቱ ድጋፎችና ባለው ቀሪ ሃብት በፍጥነት ወደ መደበኛ ሥራችን መመለስ ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል፡፡
የደረሰውን ጉዳት ሙሉ ለሙሉ መሸፈን ባያስችልም ችግሩን በጊዜያዊነት ለመቅረፍ ቢሮው እና የባሕር ዳር ከተማ ውኃ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት የመጀመሪያ ዙር የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በዚህም ከጽሕፈት ቤቱ ጎን መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ወደፊትም ክፍተቶች እየታዩ ድጋፍ የሚደረግ እና ተቋሙ ወደነበረበት እስኪመለስ ድረስ ርብርብ እንደሚያደርጉም ነው ቃል የገቡት፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤትም ለደሴ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
መረጃው፡-የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።