እናቶች የወሊድ ክትትላቸውን በጤና ተቋማት እንዲያደርጉ ሁሉም የበኩሉን ደርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

142
አዲስ አበባ፡ ጥር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም ለ35ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ በየዓመቱ የሚከበረው የጤናማ እናትነት ወር በአበበች ጎበና የእናቶች እና የህጻናት መታሰቢያ ሆስፒታል “በማንኛውም ምክንያት ከወሊድ በኋል በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶችን ሞት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንግታ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው።
ከመቶ ሺህ እናቶች መካከል ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ የተናገሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በሀገራችን በዓመት ከ11 ሺህ በላይ እናቶች ህይወታቸውን ያጣሉ፤ የእናቶች ህይወት እንዳይቀጠፍ ብዙ ሥራዎችን መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
እናቶች የወሊድ ክትትላቸውን በጤና ተቋማት እንዲያደርጉ ሁሉም የበኩሉን ደርሻ ሊወጣ እንደሚገባም ገልጸዋል።
የሚዲያ ተቋማት፣ የእምነት አባቶችና አባ ገዳዎች ተገቢውን ትምህርት ሊሰጡ እንደሚገባ እና የጤና ተቋማት 24 ሰዓት ቅድሚያ ለእናቶች እና ጤናማ አገልግሎት እንክብካቤ በመስጠት እናቶችን ሊታደጉ ይገባል ብለዋል። ጤና ሚኒስቴርም ከበፊቱ የጠነከረ ስራን በመስራት እናቶችን ለመታደግ ይተጋል ነው ያሉት።
በእርግዝና እና በወሊድ ምክንያት የሚከሰት የእናቶች ሞት በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመሆኑ ብዙ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ የተናገሩት የአዲስ አበባ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ እስከ ታች በመውረድ በጤና ጣቢያዎች ተገቢውን የህክምና ክትትል እንዲኖር እየሰራን ነው ብለዋል። ባልተገባ ሁኔታ የሚደረጉ የጽንስ ማስወረድ ድርጊቶችን በማስቆም እና ለማኅበረሰቡ ግንዛቤን በመፍጠር የሁሉም እናት የወሊድ ክትትል እና ድህረ ወሊዳቸው በህክምና ተቋማት እንዲሆን በማድረግ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:–ራሄል ደምሰው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous article“አሸባሪው፣ ዘራፊው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን የአማራና የኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን እንሠራለን” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next article❝እንሂድ አምባሰል በሽሎን እንሻገር ግሸን እንገናኝ ግማደ መስቀሉ ካረፈበት ሀገር❞