
ደብረ ብርሃን፡ ጥር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የደረሱ ጉዳቶችን በተመለከተ የሠራውን ጥናት ለውይይት አቅርቧል። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት በሰላም ጊዜ ትውልድ የሚቀርፁ በችግር ወቅት ደግሞ መፍትህሔ የሚያመጡ መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው፣ ወራሪውና ዘራፊው የትግራይ ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም አንስተዋል።
የደረሰውን ጉዳት በተገቢው መንገድ ሰንዶ ማስቀመጥ የምሑራን ኀላፊነት በመሆኑ ዩኒቨርስቲው ይህንን በማድረጉ ምሥጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡ አሁን በደረሰብን ችግር መቆዘም ሳይሆን ከችግሩ መውጫ መንገዶችን በመፈለግ መልሶ ማቋቋም ላይ ሊሠራ ይገባልም ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

“አሸባሪው፣ ዘራፊውና ወራሪው የትግራይ ቡድን የአማራና የኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን እንሠራለን” ሲሉም አስታውቀዋል፡፡ ዶክተር ይልቃል አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እንዲጠፋ በእውቀት ላይ የተመሰረተ አካሄድ ልንከተል ይገባልም ብለዋል።
ዘጋቢ፡-ኤልያስ ፈጠነ-ከደብረ ብርሃን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።