❝የትምህርት ማስታወቂያዎች የትምህርት ጥራትን መሰረት ያደረጉ መሆን ይገባቸዋል❞ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ

179
አዲስ አበባ፡ ጥር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የከፍተኛ ትምርት ተቋማት ማስታወቂያ በምን መልኩ መስተናገድ አለበት በሚለዉ ዙሪያ ከመገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ጋር የጋራ ምክክር ተደርጓል። የመገኛኛ ብዙኀን ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ተስፋየ የትምህርት ማስታወቂያዎች ላይ በርካታ ክፍተቶች ይታያሉ ብለዋል።
የትምህርት ተቋማት ማስታወቂያዎች ቤተሰቦች ለልጆቻቸዉ ያላግባብ የኾነ ገንዘብ ከፍለዉ እንዲያስተምሩ አድርጓልም ሲሉ ጠቅሰዋል።
“በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዙሪያ የሚሠሩ ማስታወቂያዎች በትክክለኛው መንገድ እና በተገቢዉ ያለማጋነነን መቅረብ ይገባቸዋል” ብለዋል፡፡
የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ እንደተናገሩት የትምህርት ማስታወቂያዎች የትምህርት ጥራትን መሰረት ያደረጉ መሆን ይገባቸዋል። ተቋማቱም ለትምህርት ጥራት እና ለጥሩ ዜጋ ማፍራት ቅድሚያ በመስጠት ሊሠሩ ይገባቸዋል፤ የማስታወቂያ ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙኀንም ይህንን ታሳቢ በማድረግ መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኾነዉ የትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት ሳያደርጉ በማስታወቂያ ብቻ የበርካታ ቤተሰብን ኑሮ አዛብተዋል ብለዋል።
በሐሰተኛ ማስረጃ በማስታወቂያ ላይ የሚቀርቡ የትምህርት ተቋማትም በዝተዋልም ሲሉ ጠቅሰዋል።
የማስታወቂያ ተቋማት ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችም የተቋማትን ሕጋዊነት በተገቢነት ማረጋገጥ እና የትምህርት ጥራቱ ላይ ትኩረት ያደረገ ሊሆን ይገባዋልም ብለዋል።
የግል እና የመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቁ ዜጋን ማፍራት ቅድሚያ ትኩረታቸዉ ሊሆን እንደሚገባም ተጠቁሟል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉዑሽ-ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleየአፍሪካ ሕብረት 35ኛው የመሪዎች ጉባኤን በስኬት ለማስተናገድ በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ።ለመድረኩ  እየተካሄደ ያለው ቅድመ ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
Next article“አሸባሪው፣ ዘራፊው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን የአማራና የኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን እንሠራለን” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)