
ጥር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የአፍሪካ ሕብረት 35ኛው የመሪዎች ጉባኤና 40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባን ለማስተናገድ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን አስመልክቶ ለመድረኩ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ግምገማ አካሂዷል።
በወቅቱም ከ20 በላይ የብሔራዊ ኮሚቴው አባል ተቋማት ለጉባኤው እያደረጉ ያሉትን ቅድመ ዝግጅት አቅርበው ውይይት ተደርጓል። ቅድመ ዝግጅቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
እንግዶች ከአየር ማረፍያ እስከ ሆቴሎችና የስብሰባ አዳራሽ ደኅንነታቸው ተጠብቆ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ተግባራዊ ዝግጅቶች በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳሉ ተጠቁሟል። መሰረተ ልማቶችን መልሶ ከመጠገንና ያለምንም እንከን አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንፃር ጥሩ ሥራዎች በተቋማዊ ቅንጅት እየተሠሩ መሆኑም ተመላክቷል። ከጤና አንፃርም ኢትዮጵያ ይሄን ጉባኤ ለማከናወን ለሕብረቱ ቃል በገባችው መሰረት በተለይ ከኮሮናቫይረስ ምርመራና ህክምና ጋር በተያያዘ ጥሩ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል። በዚህም ወደ አፍሪካ ሕብረት የሚገባ ማንኛውም አካል የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት በማሳየት በመሆኑ ይሄንን የሚመጥን ምርመራም በኤርፖርት፣ ሆቴሎችና በአፍሪካ ሕብረት ግቢ እንደሚደረግም ነው የተጠቆመው።
ድንገተኛ ህመም ቢያጋጥምም የህክምና መስጫ ቦታ ከብቁ ባለሙያዎች ጋር መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።
መድረኩን የመሩት የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ኹሉም መሥሪያ ቤቶች ያከናወኑት ቅድመ ዝግጅት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰዋል። የቀሩ ሥራዎችም በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል።
መድረኩ ኢትዮጵያ ገፅታዋን አጉልታ የምታሳይበት አጋጣሚ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ጉባኤውን በስኬት አስተናግዶ ለማጠናቀቅ ብርቱ ትብብርና ጠንካራ ቅንጅት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/