“ሀገራዊ የምክክር መድረኩ የተሳካ እንዲሆን የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው” የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

132

ባሕር ዳር፡ ጥር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሊጉን የስድስት ወራት የመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

በአዳማ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የወጣቶች ሊግ የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በሊጉ የስራ አስፈጻሚ አባላት ውይይት እየተደረገበት መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሬዝደንት አስፋው ተክሌ ገልጸዋል፡፡

አቶ አስፋው አያይዞም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወጣቶች በህልውና ጦርነት ወቅት ያሳዩት ተነሳሽነት ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት ያሳዬ ነበር ያሉ ሲሆን የሊጉ አመራሮችና አባላት አውደ ውጊያ ድረስ በመሠለፍ፣ ደም በመለገስ፣ ለመከላከያ ገንዘብ በማዋጣትና በማስተባበር በማሰባሰብ፣ የዘማች ቤተሰቦችን ሰበል በመሰብሰብ እንዲሁም የአቅመ ደካማ ሰዎችን ቤቶች በመገንገባት የነበረው ርብርብ የሚደነቅና በሌሎች ልማት እንቅስቃሴዎችም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል፡፡

የነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ መንግስት ንቅናቄ ከ2 ነጥብ7 ሚሊዬን በላይ ደብዳቤዎችን ወደ ነጩ ቤተ መንግስት በመላክ የኢትዮጵያን እውነታዎች ለዓለም ለማሳወቅ ንቁ ተሳትፎ ስለመደረጉ በመደረኩ የተነሳ ሲሆን ከጦርነት በኃላ የድል ማግስት መዛነፎችን በጥንቃቄ መምራትና ማስተካከል እንደሚገባም አመላክቷል፡፡

ወጣቶች በሀገረ መንግስት ግንባታ፣ ለአካታች ሀገራዊ የምክክር መድረክ ውጤታማነት ወጣቶቸ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸውን ተገልጿል፡፡

የውይይት መድረኩም እስከ ነገ እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየጉብኝት መዳረሻዎችን በማልማት እና በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ጠቀሜታ ማሳደግ እንደሚገባ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሣኅሉ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡
Next articleየአፍሪካ ሕብረት 35ኛው የመሪዎች ጉባኤን በስኬት ለማስተናገድ በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ።ለመድረኩ  እየተካሄደ ያለው ቅድመ ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።