
ባሕር ዳር: ጥር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጥርን በባሕር ዳር የታንኳ ውድድር እና የጀልባ ትርዒት በጣና ሐይቅ ላይ ተካሂዷል፡፡
ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደው የታንኳ ውድድር እና የጀልባ ትርዒት የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው የመጡ ዳያስፖራዎች የሚኖራቸውን ቆይታ ማራኪ ለማድረግ የታለመ መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገልጿል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሣኅሉ (ዶ.ር) በባሕር ዳር ከተማ ብሎም በአማራ ክልል ያለውን እምቅ የጉብኝት መዳረሻ በማልማት እና በማስተዋወቅ ረገድ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም የሚኖረውን ምጣኔ ሃብታዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ኹነቶች እያካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል። ዛሬ የተካሄደው የታንኳ ውድድር እና የጀልባ ትርዒቱ አንዱ የዚህ አካል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ድረስ ኅብረተሰቡ በተለይ ወጣቶች በባሕር ዳር ከተማ ያለውን ጽዳት እና አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ በማድረግ ብሎም የጉብኝት መዳረሻዎችን በማልማት ለጎብኚዎች ምቹ እንድትሆን እየተደረገ ያለውን ጥረት በማገዝ ረገድ የጎላ ሚና ሊጫወቱ ይገባል ብለዋል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ብሎም በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ የተቀዛቀዘውን ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ተከታታይ መሰል ሥራዎች እንደሚከናወኑም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አስታውቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡-የማነብርሃን ጌታቸው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/