
ጥር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት ላይ በመዋጋትና በማዋጋት፣ ጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲደርስበት ያደረጉ፣ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና ካሉበት ኀላፊነት አንፃር አንድ ደረጃ ከፍ ማለት ለሚገባቸው አመራሮችና አባላት ነው የማዕረግ እድገት የተሰጠው፡፡
የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናንት ጀነራል መሐመድ ተሰማ “ማዕረግ ሲጨምር የበለጠ ኀላፊነትና ተጠያቂነት የሚጨምርበት፣ የቀጣይ ተልዕኳችሁን በላቀ ሁኔታ ለመወጣት ራሳችሁን የምታዘጋጁበት እና የምትወጡበት ነው” ብለዋል፡፡

ለሀገር እና ለሕዝብ ታማኝ በመሆን ግዳጅን በፅናትና በጀግንነት መወጣት እንደሚገባ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
“መንግሥትና ሕዝብ የሰጡንን ተልዕኮ በድል አድራጊነት ፈፅመን ለቀጣይ ግዳጅ እየተዘጋጀን ባለንበት ወቅት የተሰጣችሁን የማዕረግ እድገት ሽልማት ተጨማሪ አቅም ስለሚሆናችሁ በየወቅቱ ሊያጋጥማችሁ የሚችለውን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መሰናክሎችን ለማለፍ የሚያስችል ብቃት፣ የአመራር ሳይንስና ጥበብ እንዲሁም ፈጠራ በመጠቀም በውጤታማነት መወጣት ይጠበቅባችኋል” ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/