
ባሕር ዳር፡ ጥር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ አፍሪካ በኖርዝዌስት ፕሮቪንስ ራስተንበርግ ከተማና በአካባቢ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ በቆራጥነት ለተፋለመው ጀግናው የወገን ጦር እና በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን ያሰባሰቡትን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር አስረክበዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት በፕሪቶሪያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ የዳያስፖራ ስራ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው መኬቦ ለተበረከተው የገንዘብ ድጋፍ ማኅበረሰቡንና አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አመስግነዋል። እንደሀገር የተጋረጠብን የህልውና አደጋ እስኪቀረፍ እና ጉዳት ላይ የሚገኙ ወገኖችን ወደ መደበኛ ኑሯቸው ለመመለስ መንግስት ለሚያደርገው የመልሶ ማቋቋም ጥረት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ድጋፋን ላበረከቱት በራስተንበርግ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ እና የኮሚኒቲ አመራሮችና አስተባባሪዎች በኤምባሲዉ የተዘጋጀዉ የዕውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል::


በአጠቃላይ በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አሸባሪው ትህነግ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ ለተፋለመው ጀግናው የወገን ጦርና እና ለተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እስከአሁን ከ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡ ተገልጿል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።