አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን ጦርነት መክፈቱን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

167

ባሕር ዳር፡ ጥር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአፋር ክልል ውስጥ ገብቶ የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት ለማካካስ በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በአብአላ እና በመጋሌ ወረዳ የከፈተውን ውጊያ አጠናክሮ መቀጠሉን የአፋር ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ምንም ዓይነት ሰብዓዊነት እና ርህራሄ የሌለው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በንፁሀን ዜጎች ላይ ከባድ መሳሪያ ጭምር በመተኮስ እያሸበረ ይገኛል ብሏል።
ሁሌም ከትንኮሳ አርፎ የማያውቀው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለዘመናት የቆየውን በድንበር የሚዋሰኑ የአፋር እና የትግራይ ሕዝቦችን ግንኙነት ከምንም ሳይቆጥረው ሁለቱን ሕዝቦች በማጋጨት የማይረባ ትርፍ ለማግኘት ሌት ተቀን እየጣረ ይገኛል።
እያደረሰ ባለው ጥቃትም የአፋር ንፁሃንን ዒላማ በማድረግ የሽብር ተግባሩን በማስፋት ላይ ነው።

በዛሬው ዕለት እንኳን በኪልበቲ ረሱ ዞን በተለያዩ ቦታዎች የአፋር ክልልን ወሰን ጥሶ በመግባት በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በመክፈት በርካታ ንፁሀንን ለጉዳት ዳርጓል።

በአፋር በተለያዩ አካባቢዎች ወረራ አካሂዶ በሁሉም ግንባሮች ሽንፈትን አስተናግዶ የወጣው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አሁንም እንደ አዲስ በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በከፈታቸው ግንባሮች የምድር ድሮኖቹ አስፈላጊውን መከታ እና ማጥቃት እያካሄዱ ነው ብሏል፡፡ የምድር ድሮኖቹ መከታ እና ማጥቃቱ የጁንታውን እብደት የሚያመክን በመሆኑ አሸባሪው ቡድን ዘልቆ ገብቶ ለመውረር ያስገባውን ኃይሉን አስቀድሞ ሊያወጣ ይገባል ሲል የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ባወጣው መግለጫ አሳሰቧል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleከአምራች ዘርፉ ከ238 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ የስድስት ወራት አፈጻጸሙን በደሴ ከተማ እየገመገመ ነው።
Next articleበደቡብ አፍሪካ ኖርዝዌስት-ራስተንበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራዊ ጥሪ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡