
ባሕር ዳር፡ ጥር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት 6 ወራት ከአምራች ዘርፉ 238 ነጥብ 267 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከአምራች ዘርፉ 265 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የእቅዱን 89 ነጥብ 8 በመቶ ገቢ የተገኘ ሲሆን አፈጻጸሙ በአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ50 ነጥብ 77 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው ተብሏል፡፡
ኢንዱስትሪው ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ካለው አስፈላጊነት አኳያ ከላይ እስከ ታች የተናበበ አደረጃጀት እንዲኖረው መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በወሰነው መሰረት ባለፉት 6 ወራት አደረጃጀቱን የማጠናከር ሥራ ሲሰራ መቆየቱን የኢንደስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡
ዘርፉ በበርካታ ሀገራዊ ችግሮች ውስጥ ቢሆንም የውጪ ምንዛሪ ገቢን ለማሻሻል በተሰሩ ሥራዎች የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የጠቀሱት ሚኒስትሩ የገቢ ምርትን ለመተካት በተሰሩ ሥራዎች ትልቅ ውጤት መምጣቱንም ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴሩ የ6 ወራት አፈፃጸሙን ከክልልና ከተማ አስተዳደር የዘርፉ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ፣ ከተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻዎች ጋር በደሴ ከተማ እየገመገመ ይገኛል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።