በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይዎት አለፈ፡፡

194

ጥር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከባሕር ዳር ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ለግዳጅ ከባሕር ዳር መነሻውን ያደረገው የሕዝብ ማመለሻ አውቶብስ በደረሰበት አደጋ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ታውቋል፡፡

የደረሰውን የትራክ አደጋ በተመለከተ ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የድሃና ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው ለግዳጅ ከባሕር ዳር የወጣው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በመንገድ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ አደጋው እንደደረሰ ነው የተናገሩት፡፡ አደጋው የደረሰው መለያ ቁጥሩ 11300፣ የጎን ቁጥሩ 2527 የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ጉዳቱ የደረሰው ከአምደወርቅ ወጣ ብሎ አቦ መገጠንያ መንገድ በምትባል ሥፍራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ በግምት 200 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ መግባቱንም ተናግረዋል፡፡ በደረሰው አደጋም 20 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች ጋር ቆይታ እንዳደረጉ የተናገሩት ኃላፊው ከእብናት ወደ አምደ ወርቅ ሲጓዝ ብዙ ሰው እንደነበርና ከአምደወርቅ ሲያልፉ ግን ሰው ያልነበረባቸው ወንበሮች እንደነበሩ ነግረውኛል ነው ያሉት፡፡ ለአደጋው ምክንያት ፍጥነት እና የመንገዱ መጎዳት ሳይሆን እንዳልቀረም ተናግረዋል፡፡ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ፎቶ፡- ዋግኽምራ ኮምዩኒኬሽን

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ተነጣጥሎ ከመቆም በሕብረት መቆም የአሸናፊነት ሚስጥር መሆኑን አይተናል፤ በተገኘው ድልም እንዳንታበይ እና እንዳንዘናጋ ድሉን ጠብቆ እና ተንከባክቦ ማስቀጠል ተገቢ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየጋምቤላ ክልል በአማራ ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ።