
ጥር 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከሱዳን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን መሥራት እንደሚገባን መግባባት ላይ ደርሰናል ሲሉ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ.ር) ገለጹ።
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ዶክተር አብርሃም አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
የጄኔራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎን የኢትዮጵያ ቆይታን በተመለከተ ዶክተር አብርሃም ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያና በሱዳን የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
“አብረንና ተቀራርበን መሥራት እንደሚገባን ተግባብተናል” ሲሉም ገልጸዋል።
ትናንት አዲስ አበባ የገቡት ጄኔራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።
ጄኔራሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ከሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶ.ር) እና ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/