አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተቀጥቅጦ የተቀበረበት የካራ ምሽግ ድል እየተዘከረ ነው።

369

ደብረ ብርሃን፡ ጥር 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የሚገኘው ታሪካዊዉ ካራ ምሽግ ወራሪው ቡድን የተቀበረበት ነው።

ይህ ታሪካዊ ቦታ ከዮዲት ጉዲት ዘመን ጀምሮ አምስት ዋና ዋና ጦርነቶች ተካሂደውበታል።
በዮዲት ጉዲት፣ በግራኝ መሐመድ፣ በጣሊያን ወረራ፣ በደርግና ወያኔ እንዲሁም በህልውና ዘመቻው ጦርነቶች ተካሂደውበታል።

የሚዳ ወረሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘሪሁን ኀይለ ጊዮርጊስ በካራ ምሽግ በሁሉም ጦርነቶች ኢትዮጵያ ማሸነፏን ተናግረዋል።

በሕልውና ዘመቻው በታሪካዊዉ ካራ ምሽግ የተገኘው ድልም ዛሬ እየተዘከረ ይገኛል።

መከላከያ ሰራዊቱን ወክለው የተገኙት ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንን ካራ ምሽግ ላይ የተቀዳጀነው ድል ለኢትዮጵያ መቀጠል ሁነኛ የድል መንገድ ነበር ብለዋል።

ዝክረ ካራ ምሽግ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የመንግስት የሥራ ኀላፊዎችን ጨምሮ የሰራዊቱ አባላት በተገኙበት በመስክ ጉብኝትና በፓናል ውይይት ታስቦ ውሏል።

ዘጋቢ:–ኤሊያስ ፈጠነ–ከካራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝ኢትዮጵያ በታላቁ ሩጫ ላይ ናት!❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር
Next article❝ግዮን ወተት ኾኖ ገነትን ካጠጣት የግዮን መነሻ ኢትዮጵያ ምንድን ናት?❞