
አዲስ አበባ፡ ጥር 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ምዕራባዊያን በመረጃ በኩል የሚፈጥሩት ተዕፅኖ ጉዳቱ ዘርፈ ብዙ መሆኑንና ኢትዮጵያዊያን በልኩ መመለስ አለብን ብላለች። ጋዜጠኛ ሄርሜላ “እኔም ስለሀገሬ የሚወሩትን የሃሰት መረጃዎች በማስተካከል ትግሌን አጠናክሬ እቀጥላለሁ፤ እኔም እናቴም ስለ ኢትዮጵያ የተሳሳተ መረጃ ህወሃትን ደግፈን እንድናሰራጭ ብዙ ተዕፅኖ ሲደረግ ነበር፤ ነገር ግን እኔና እናቴ ለእውነት እና ለሀገራችን ነበር የወገነው፤ ለእውነት ስንቆምም በርካታ ተዕፅኖዎች ነበሩ” ብላለች።
ከሀገር የሚበልጥ የለም ያለችው ጋዜጠኛ ሄርሜላ ተዕፅኖዎች እንደማያስቆሟት፣ የጀመረችውን የኖሞር ዘመቻ ከጓደኞቿ ጋር አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች።
ሁሉም ጋዜጠኛ ለእውነት እና ለህዝብ መቆም እንዳለበትም አስገንዝባለች፡፡
ትግሏ ከእውነት ጋር እንጂ ከፖለቲካ ጋር እንዳልሆነም ገልጻለች።
ጋዜጠኛ ሄርሜላ የአንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት ተዕፅኖ መቋቋም የሚችል፤ ስለኢትዮጵያ መረጃ የሚያቀብል ተዕፅኖ ፈጣሪ ዓለማቀፍ ሚዲያ እንዲፈጠር እና እሷም ለሀገሯ የበኩሏን ለማበርከት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
0
People reached
58
Engagements
Boost post
51
5 Comments
2 Shares
Like
Comment
Share