የአፋር ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የሀገር ሽማግሌዎች የአፋር ሕዝብ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ላይ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላለፉ።

121
ጥር 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፋር ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የሀገር ሽማግሌዎች አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን “ምላዛት እና ዳንዲ በሚባሉ ቦታዎች የአፋር ልዩ ኃይል ገብቷል” በማለት ለአፋር የሃይማኖት አባቶች እና ሀገር ሽማግሌዎች መፍትሔ እንዲፈልጉ መግለጫ ማውጣቱን በማስመልከት የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የሀገር ሽማግሌዎች መግለጫ አውጥተዋል።
የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የሀገር ሽማግሌዎችም አሸባሪው ቡድን ”በከባድ መሳሪያ በየቀኑ የንጹሐን ነፍስ እያጠፋ ፣ በውሸት ተወረርን በማለት እና ሰላም ፈላጊ መስሎ በመቅረብ የተለመደ ማደናገሪያውን ማቅረቡ በፍፁም ተቀባይነት የለውም” ሲሉ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
“የትግራይ ወራሪ ኃይል ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ለአፋር የሃይማኖት አባቶች እና ሀገር ሽማግሌዎች መፍትሔ እንድናፈላልግ በመግለጫ የጠየቀ ቢሆንም በተጠቀሱት ቦታዎች አንድም የአፋር ልዩ ኃይል የለም” ያለው መግለጫው “እየወረሩ ተወረርን፤ ንጹሐንን በጅምላ እየጨፈጨፈ ተጨፈጨፍን ማለት የተለመደ የአሸባሪው ኃይል ዓለምን ማደናገሪያ መንገድ ነው” ብሏል።
የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በመግለጫቸው እንዳስታወቁት የአፋርም ኾነ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጀመሪያ ምርጫው ሰላም ቢሆንም የትግራይ ወራሪ ኃይል ግን ፀረ ሰላም መሆኑን ሀገር በማተራመስ፣ ንጹሐን አርብቶ አደሮችን በመጨፍጨፍ፣ የመንግሥት እና የሃይማኖት ተቋማትን በማውደም ማንነቱን የገለጸ በመሆኑ አሁንም ለዳግም ወረራ ከዳሎል እስከ ያሎ የአፋር ወሰን ላይ ባሉ አካባቢዎች ያስቀመጠውን ወራሪ ኃይል በአስቸኳይ እንዲያስወጣ አሳስቧል።
ይህ የማይሆን ከሆነ ግን “የአፋር ሕዝብ ኢትዮጵያን እንዳታፈርሱ ያደናቀፋችሁ እና በአፋር ምድር ደምስሶ ያስቀራችሁ ጀግናው ሕዝብ ዛሬም አለ” ብሏል በመግለጫው።
“አፋር አልፎ የሰው ወሰን አይወርም፤ የራሱንም አያስወርርም፤ ኢትዮጵያ ስትፈርስም ዝም ብሎ አያይም፤ እስከ መጨረሻው ይፋለማችኋል” ሲሉ የአፋር ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት እና የሀገር ሽማግሌዎች ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ዘገባው የአፋር ክልል ብዙኀን መገናኛ ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous articleበኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደመውን የወሎ ዩኒቨርስቲ እና የደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመለከቱ።
Next article❝የኢትዮጵያን ገጽታ ማበላሸት የፈለጉ አካላት የጥምቀትን በዓል በመረበሽ ተልዕኳቸውን ለማሳካት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካላቸውም❞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት