በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደመውን የወሎ ዩኒቨርስቲ እና የደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመለከቱ።

203
ተቋማቱ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አምባሳደሩ ቃል መግባታቸውም ተገልጿል።
ደሴ: ጥር 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በወሎ ዩኒቨርስቲ እና ደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፈጸመውን ዘረፋና ውድመት በኢትዮዽያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ ተመልክተዋል።
የደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ኃይማኖት አየለ ተቋሙ ወደ አገልግሎት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ከፍተኛ የሆነ የቁሳቁስ ችግር መኖሩን አስረድተዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሆስፒታሉ ከ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የንብረት ዘረፋና ውድመት እንዳደረሰ ለአምባሳደሩ ገልጸዋል።
ላጋጠመን ጉዳት ምላሽ ለመስጠት ቃል የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ያሉት ዶክተር ኃይማኖት ፈጥኖ ምላሽ በመስጠት በኩል መዘግየት መኖሩ ሥራችንን ለመፈጸም አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል።
የወሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ በበኩላቸው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዩኒቨርሲቲውን ሙሉ በሙሉ ቢያወድመውም የመማር መስተማሩን ሥራ ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የደረሰውን ዘረፋና ውድመትም ለአምባሳደሩ ገልጸዋል።
አምባሳደሩ በመገናኛ ብዙኀን ብቻ ይመለከቱት የነበረውን ውድመት በአካል ተገኝተው መመልከታቸው እና እውነታውን መረዳታቸው አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለውም ዶክተር መንገሻ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ
ለዩኒቨርስቲውና ለደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
ዘጋቢ:- ደጀን አምባቸው – ከደሴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
Previous article❝የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲኖር ያደርጋል❞ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ
Next articleየአፋር ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የሀገር ሽማግሌዎች የአፋር ሕዝብ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ላይ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላለፉ።