❝የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲኖር ያደርጋል❞ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ

125

ጥር 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲኖር እንደሚያደርግ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንቷ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ በሕገ መንግሥቱ መሠረት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ማቋቋምያ ዐዋጅን ባለፈው ሳምንት መፈረማቸውን አስታውቀዋል።
መፈረም ኃላፊነቴ ቢሆንም የእውነተኛና አካታች ብሔራዊ ምክክርን ቁልፍነት ስለማውቅ፣ ስለሠራሁበት፣ ውጤቱንም ስላየሁ አምንበታለሁ ነው ያሉት፡፡
ምክክሩ በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲኖር ያደርጋል፣ ሐሳብን በግድ መጫንን፣ ጦር መማዘዝን፣ ሕዝብንና ሀገርን አደጋ ላይ መጣልን ከመሳሰሉ አደጋዎች እንደሚያድንም ተናግረዋል፡፡
“የንግግር፣ የመደማመጥ፣ የመከባበር አዲስ ባሕል ይፈጥራል፣ እንደ እኛ ከአውዳሚ ጦርነት ማግስት ለሚገኝ ሀገር ጠቀሜታው ግልጽ ነው” ብለዋል።
ይህንን አገራዊ ምክክር እንዲመራና እንዲያካሂድ የሚቋቋመው ኮሚሽን አባላት ጥቆማ ሲካሄድ መቆየቱን በማንሳት፥ ለአንድ ሳምንት ከተራዘመ በኋላ ጥር 13/2014 ዓ.ም እንደሚያበቃም ጠቁመዋል።
ለኮሚሽነርነት የተጠቆሙ ሴቶች ቁጥር አነስተኛ ይሆናል ብዬ እሰጋለሁ ያሉት ፕሬዚዳንቷ ሴቶች መጠቆም አለባቸው ብለዋል፡፡
ጦርነቱ በሴቶች ላይ ያስከተለው ሁኔታ ገና በብዙ የሚታይ ነው፤ ሴት ሰለባ ብቻ ሳትሆን የመፍትሔ አካል መሆንዋ ከግንዛቤ መወሰድ አለበት ያሉት ፕሬዚዳንቷ የሴት ኮሚሽነሮች መኖር ካላቸው አጠቃላይ ኃላፊነት ጋር የእነዚህም ሴቶች ድምጽ ይሆናሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በቀረው ጊዜ የወጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሴቶችን ኅብረተሰቡ እንዲጠቁም ፕሬዚዳንቷ
ጥሪ አቅርበዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ጎንደር አባ ጃሌ ከግንቡ ደርሼ፤ ያለዕድል አይሆንም መጣሁ ተመልሼ።”
Next articleበኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደመውን የወሎ ዩኒቨርስቲ እና የደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመለከቱ።