በፊንላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

257

ባሕር ዳር: ጥር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ)በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ በማድረግ ለሀገራቸው አለኝታነታቸውን እያስመሰከሩ ይገኛሉ።

ዛሬም በፊንላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመረባረብ በአማራ ክልል ለተጎዱ ወገኖች 1 ሚሊዮን 116 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል። ድጋፉን ያስተባበሩትና ያስረከቡት ዶክተር ትዕግሰት ቸርነት ከድጋፉ በተጨማሪ በክልሉ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እንደሚደግፉም ነው የጠቆሙት።

በፊንላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአሁን በፊትም በአፋር ክልል በመገኘት ለክልሉ መንግሥት ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

የአማራ ክልል የሚያከናውናቸውን ሁለንተናዊ የልማት ተግባራት እንደሚደግፉም ዶክተር ትዕግስት ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በተባበረ የወገን ጦር ክንድ ተደምስሷል ብለዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በትግሉ በመሳተፍ አለኝታነታቸውን አስመስክረዋል ነው ያሉት።

በፊንላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ማድረጋችሁ አርዓያነታችሁን ያሳያል ነው ያሉት።

ሌሎች አካላትም የተጎዱ ወገኖችን በመደገፍና መሰረተ ልማቶችን በመገንባት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ጦርነቱ ኢትዮጵያ ያልፈለገችው እንደኾነና የሽብር ቡድኑ አሁንም ትንኮሳውን እንዳልተወ አመላክተዋል። አሁንም ቢሆን በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ዘብ መቆም እንዳለባቸው አፈ ጉባዔዋ አሳስበዋል።

አፈጉባኤዋ ድጋፉን ላስረከቡት አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ከተማዋ በኢንቨስትመንት ተደራሽት ብቻ ሳይሆን ለነዋሪዎቿ ምቹ በመሆን ተመራጭ እንደትሆን እየሰራን ነዉ” የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ካሳሁን እምቢዓለ
Next article“ጎንደር አባ ጃሌ ከግንቡ ደርሼ፤ ያለዕድል አይሆንም መጣሁ ተመልሼ።”