“ልደትን በላልይበላ” እና “ጥምቀትን በጎንደር” በሰላም ማጠናቀቅ የአማራ ሕዝብን የሥነ ልቦና ልዕልናን የሚያሳይ ነው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

183

ጎንደር፡ ጥር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን ከአብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢዎች ተደምስሶ በወጣ ማግስት ክልሉ ሁለት ዐበይት ሃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ በዓላትን በስኬት አጠናቋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት እና የውጭው ክንፍ ደጋፊዎቻቸው ሀገሪቱ ብሎም ክልሉ ሰላም አልባ እና የጦርነት ቀጣና ለማስመሰል ብዙ ቢያወሩም በዓላቱ ግን ፍጹም ሰላማዊ ኾነው ተጠናቀዋል። የበዓላቱን በሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኅላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ መግለጫ ሰጥተዋል።

“ልደትን በላልይበላ” ማክበር ለበርካቶች የማይታመን ነበር ያሉት አቶ ግዛቸው ሙሉነህ “ጥምቀትን በጎንደር” ያለምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁ ደግሞ ለሀገሪቱ ብሎም ለክልሉ ዘርፈ ብዙ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ክልሉ ላለፉት ወራት የቆየበትን የኅልውና ፈተና ማንም ያውቀዋል ያሉት አቶ ግዛቸው “ልደትን በላልይበላ እና ጥምቀትን በጎንደር በሰላም ማጠናቀቅ የአማራ ሕዝብን የሥነ ልቦና ልዕልና የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

ከሀገር ውስጥ ተላላኪዎች እስከ ውጭ ሴረኞች በክልሉ ሰላም የሌለ ለማስመሰል ብዙ ጥረት ተደርጓል ያሉት አቶ ግዛቸው የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች፣ የክልሉ ሕዝብ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ተሳትፎ የጠላትን ምኞት አክሽፏል ነው ያሉት።

የክልሉ መንግሥት በዓላቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል ብለዋል አቶ ግዛቸው።

በዓላቱ በሰላም መጠናቀቃቸው ለክልሉ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ያሉት አቶ ግዛቸው ከኹነቶቹ ጎን ለጎን የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች እና የፌዴራል ሚኒስትሮች ከኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር የሚመክሩበት እድል ተፈጥሯል ብለዋል።

ምክክሩም ለኢንቨስትመንት እድል ፈጠራ እና የቱሪዝሙን ዘርፍ ለማሳደግ ጥቅሙ የጎላ ነው ተብሏል።

በቀጣይም የግዮን በዓል ጥር 13/2014 ዓ.ም እና የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ጥር 23/2014 ዓ.ም ይከበራሉ ያሉት አቶ ግዛቸው ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው -ከጎንደር

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ከሳምንት በኋላ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
Next article“ጊዜው የህዳሴው ግድብ ለሶስቱ ሀገራት የሰላም፣ የትብብር እና የአብሮ መኖር ተምሳሌትነቱን የምናሳይበት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ