“ነፃነትን አጥቶ የነበረ ህዝብ በነፃነት ሲያከብር ማየት ነብስን ያስደስታል” የወገን ጦር አባላት

207

ሁመራ፡ ጥር 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ብዙ በደልና ግፍ ለሠላሳ ዓመታት ተሸክሞ በባርነት ቆይቷል። ይህ ህዝብ ሲታገል ኑሯል።

የአሸባሪውን የክፋት ሴራ ተከትሎ ጀግናው የወገን ጦር ከህዝቡ ጋር በመሆን ወልቃይትን ነፃ ማድረጉም በብዙዎቻችን ህሊና የማይረሳ ድንቅ ድል ነው።

ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞንን የነፃነት ካባ ለማልበስ በተካሄደው የህልውና ዘመቻ ብዙዎች ደማቸውን አፍስሰዋል፤ አጥንታቸውን ከስክሰዋል። ታዲያ በወገኖቿ ተጋድሎ የነፃነት አየር መተንፈስ የጀመረችው የወልቃይት ጠገዴ ምድርም የተነጠቀችውን ማንነት አስመልሳ የክት ልብሷን አጥልቃ የጥምቀትን በዓልን እያከበረች ትገኛለች።

ነፃነትን አጥቶ የነበረ ህዝብ በነፃነት ሲያከብር ማየት ነብስን ያስደስታል ሲሉም በሁመራ ከተማ የጥምቀትን በዓል በማክበር ላይ የሚገኙ የወገን
ምክትል ሳጅን ሙሉሰው ዳኘው የተከፈለው መስዋእት ተከፍሎ ህዝቡ በነፃነት በዓሉን ሲያከብር በማየቱ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

የዚህን ህዝብ ነፃነት አስጠብቆ ለመዝለቅና የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግሯል።

“የህዝቡን ደስታ ማየት ይበልጥ ለድል እንድንተጋ አድርጎናል” ያሉን ደግሞ ምክትል ኢንስፔክተር ፀዳሉ ባየ ናቸው።

ከዚህ ቦታ ላይ እንዳልተረገጡ እንባቸው እንዳልፈሰሰ ሁሉ ያንን ሁሉ ዘመን ታግለው እንዲህ በደስታ በጭፈራ ሲያከብሩ ማየት ነብስን በሀሴት ይሞላል ብለዋል።

ሌላኛው የወገን ጦር አባል የሆነው ጌታቸው አደም ተረግጦ የነበረ ህዝብ እንዲህ በደስታና በፍቅር ሲያከብር ማየት ትልቅ ድል ነው ብሏል።

የወገን ጦር አባላቱ የህዙቡን ነፃነት አስጠብቆ ለመዝለቅ ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆናቸውን ለአሚኮ ተናግረዋል። ህብረተሰቡም በተገኘው ድል ሳይዘናጋ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

ያየህ ፈንቴ ከሁመራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአበቅ የለሽ ጥምቀትን ያለእንከን!
Next articleቃና ዘገሊላ